0
Posted April 17, 2014 in Amharic news
 
 

የዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በተለያዩ ከተሞች ያሉ የድርጅቱ ተወካዮችን አስመረጠ፥


የዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ቅንጀት ይዞት የተነሳዉን ራእይ ላይ በመመርኮዝና በመፅናት የዜጎች እኩልነት፣ነፃነትና ሰብአዊ መብቶች የሚከበርበትና ሕዝብ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ቅድሚያ የሚሰጠዉ አብይ ጉዳይ መሆኑን የሚያምን ድርጅት ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ አምባገነናዊ ስርዓትን በማስወገድ ፍትህ፣እኩልነትና ዱሞክራሲ የሰፈነበት ስርዐትን ለማስፈንና ለመገንባት የሚደረገዉን ትግል በታማኝነትና በቁርተኝነት ይደግፋል እንዲሁም ከላይ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ያሟላሉ ብሎ የሚያምንባቸውን ድርጅቶች በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር የተደራጁ ድርጅቶችና በጠቅላላ ጉባኤዉ አብዛኛ ድምጽ የተደገፉ፤ በብሄራዊ አንድነትና በመድብለ ፓርቲ የሚያምኑ፣ ግልጽና ዲሞክራሲያዊ አሰራር የሚከተሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን ይደግፋል።

ድርጅቱ ዋና ቢሮው በኖርዌይ ኦስሎ ሲሆን በአሁኑ ሰአት በሶስት በተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች ቅርንጫፍ ያለው ሲሆን የቅርንጫፍ ተወካዮቻችንንም የሚደራጁት በድርጅቱ የድርጅት ጉዳይ ክፍል ሆኖ በበላይነት የሚያስተዳድረውም  የዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ነው፥፥

በዚህም መሰረት ከታች የተዘረዘሩት የየከተሞቹ የድርጅታችን ተወካዮች ሆነው እንዲያገለግሉ ተወስኗል፥፣

ስታቫንገር

  1. አቢዩ ጌታቸው                      ሰብሳቢ
  2. አብዩ ኑር አማረ                     ፀሃፊ
  3. ትግስት ታደሰ አሰፋ               የህዝብ ግንኙነት

በርገን

  1. አንተነህ አማረ                      ሰብሳቢ
  2. ማርቆ ገ/ማሪያም                 ፀሃፊ
  3. ዳዊት እያዩ አብርሃ               የህዝብ ግንኙነት

ትሮንድሃይም

  1. አስማማው ተሻማሁ                   ሰብሳቢ
  2. ሚሊዮን አበበ መኮንን                ፀሃፊ
  3. ራሔል ኤፍሬም                         የህዝብ ግንኙነት

የዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

አፕሪል 17/2014