0
Posted February 16, 2014 in Amharic news
 
 

ተዋርዶ መገዛት ይብቃን!


የወያኔ ሹማምንትና አደርባይ ሎሌዎቻቸው አንገቱን አስደፍተው የሚገዙትንና የሚዘርፉትን ህዝብ ይበልጥ ስብእናውን አዋርደው ሊገዙት ለምን እንደሚፈልጉ የማይገባን ጥቂቶች አይደለንም። እነዚህን ግፈኞች ቀረብ ብሎ ላያቸው ግን ይህ ድርጊታቸው እንቆቅልሽ አይደለም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝብ አይሰማንም ብለው በር ዘግተው ከሚያካሂዷቸው ጉባኤዎች እያፈተለኩ የሚወጡ የቪዲዮና የድምጽ መረጃዎች የነዚህን ግፈኞች ስነ ህሊና ግልጽ አድርገው ያሳያሉ።

ከወራት በፊት የሶማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት የሀገር ሽማግሌ ሰብስቦ የወያኔ አላማ ከእሱ ጎሳ ጋር ተባብሮ ሌላውን ብሄረሰብ የበታች አድርጎ መግዛት መሆኑን ሲናገር የሚያሳይ ቪዲዮ ተመልክተን ነበር። የክልሉን ህዝብ የሚጨፈጭፈው ለዚህ ሲባል መሆኑን ለማሳመን ነበር በሩን ዘግቶ የተናገረው።

ሰሞኑን ደግሞ አንድ የአማራ ክልል የወያኔ ሹምና ሎሌ ልከአንደ እንደሶማሌው ሹም ካድሬዎቹን ሰብስቦ በአማራው ህዝብ ላይ ተሳለቀ፤ ለ እግራቸው ጫማ የላቸውም በሚላቸው የአማራው ተወላጅ ላይ ለሰሚ በሚሰቀጥጥ ቋንቋ ያወርደው የነበረ ስድብ የሚነግረን ተጨማሪ ነገር ተመሳሳይ የወያኔን ምንነትን ነው።

እነዚህ ግፈኞች በህዝብ ላይ የሚሰሩትን አዋርዶ የመግዛት ግፍና ዝርፊያ አሳምረው ያውቃሉ። ከዚህበላይ ደግሞ የዚህ ሁሉ ንቀትና ጥላቻ ሰለባ የሆነው ህዝብ እንደሚጠላቸውና ቀን እንደሚጠብቅላቸው ያውቃሉ። ስለዚህም ህዝቡን ይፈሩታል። ከፍርሃታቸው የሚያስታግስላቸው ህዝቡን ይበልጥ ቅስሙን ለመስበር ከቻሉ ስለሚመስላቸው በተዘጋ ቤት ውስጥ እየተሳለቁ ያስጨበጭባሉ።

የወያኔ ሹማምንት የህዝብ ብሶትና እሮሮ ማየሉን ሲሰሙ መልሰው ህዝቡን የሚሰድቡትና የሚያጠቁት፣ እንዲሁም ግንቦት 7 ሲጠነክርባቸውና የመውደቂያ ቀናቸው ሲያስቡ አሸባሪ ብለው የሚሸበሩትም ለዚህ ነው።

ህዝቡ ቅስሙ ከተሰበረ ሰላም ያገኙ ይመስላቸዋል። ወያኔዎችና የሲቪል ሰርቪስ ሎሌዎቻቸው በር ዘግተው በተሰበሰቡ ቁጥር ይህንን ፍራቻቸውን የሚያስታምሙት ህዝቡን ቅስሙን መስበራቸውን ለማረጋገጥ በሚያካሄዱት ወይይት ነው። ለዚህ ነው ህዝባችን እርስ በርሱ የሚባላበትን፤ እርስ በርሱ የጎሪጥ የሚተያይበትን መንገድ ሲቀይሱ የሚውሉት በዚህ ምክንያት ነው።

ወያኔዎች በየክልሉ እንደ አለምነው መኮነን አይነት ከጭንቅላታቸው፣ከህሊናቸው ይልቅ አፋቸው የሚቀድም ጥራዝ ነጠቅ ሎሌዎችን የሚያሰማሩትም የህዝብን ቅስም የሰበሩ አየመስላችዉ ነው::

ወያኔና ሎሌዎቹ ህዝብንየሚያታልሉበት ካርድ ከእንግዲህ አልቋል። አዋርደውናል፣ ገድለውናል፣ አስረውናል፣ አስርበውናል፣ ለስደት ዳርገዉናል፣ አለያይተውናል። ከዚህ በላይ ምን ሊያደርጉን ይችላሉ? ስለዚህ ቀኑ መሽቶባቸዋል እናበፍጥነት  ሊወገዱ ይገባል።

በዚህ ወሳኝወቅት ሁሉምየኢትዮጵያዊእንደ አንድ ህዝብ በአንድ ላይ በመነሳት የወያኔ ጉጅሌና አጎብጓቢ ሎሌዎቻቸው ያዘጋጁልንን ወጥመድ መስበርና ክብራችንን ማስመለስ ይኖርብናል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተዘጋው የወያኔ በር እየተዋረደ፣ እየተገረፈ ነውና።

ግንቦት 7 እንደሁልግዜው ዘላቂ መፍትሄ የሆነው ዴሞክራሲያዊ አንድነታችን እንዲጎለብት፣ ማንነታችን ክብራችን እንጂ መሳለቂያ እንዳይሆን በተባበረ ሃይላችን የክብራችን ባለቤት እንድንሆን ጥሪውን ያቀርባል።

በተባበረ ሃይላችን ክብረ-ስብእናችንን እናስመልስ! ተዋርዶ መኖር ይብቃን! በቃ!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!