0
Posted March 16, 2013 in News
 
 

መልስልኝ ታማኝ፡ ከማተቤ መለሰ ኦስሎ


መልስልኝ ታማኝ

ዛሪ ልጠይቅህ ወሪው በአለም ይናኝ፣

ባስታወስሁህ ቁጥር አለ የሚሰማኝ፣
እንዴት ተሳሰሩ ኢትዮጵያና ታማኝ?
በናትህ ማሕጸን ገና በጅምሩ፣
በጥንስስ እያለህ ሳይነካህ አየሩ፣
ተዋህዶህ ይሆን የእናት ሀገር ፍቅሩ?
ወይንስ ስትወለድ ሲቆረጥ እተብትህ፣
ገፍትሮ አስወጥቶህ የዘጠኝ ወር ቤትህ፣
አቅፋ ስትስምህ እማምዬ እናትህ?
ነው ቀኑ ሲጨምር ሲመሽም ሲነጋ፡
ብይ ስትጫወት ከጓደኞችህ ጋ፡
ከፉደጉን ሳትለይ እያለህ በጭልጋ?
ወይንስ ስትጀምር ፊደልን ቆጠራ፡
አዲስ ዘመን ገብተህ እውቀትን ስትቀራ፣
መቸ ተጋባችሁ ከሀገር ፍቅር ጋራ?
ድንገት ጋይንት ይሆን እዚያ ነፋስ መውጫ፣
ከጀግኖች መፍለቂያ ከባለጌው መውጫ፣
በወጉ ሳይገባህ፡ የህይወት በእሩጫ?
ወይንስ ጎንደር ላይ ነው ጃንተከል ዋርካው ስር፣
ደርሶ ጉብ በማለተ ከላይ እንደ ንስር፣
ኢትዮጵያዌነት ጋር ያረገህ እስር ስር?
ጣና ሀይቅ እንዳይሆን ስትዋኝ ከባሀሩ፣
ሲሞቅ ሲቀዘቀዝ ሲቀየር አየሩ፣
የተጠናወተህ የእናት ሃገር ፍቅሩ?
ዛሪ መልስልኝ ታማኙ ወንድሜ፣
ሁሌ የማስበው እንዲፈታ ህልሜ።
ሁሌ የማስበው እንዲፈታ ህልሜ።

ማተቤ መለሰ ተሰማ
10.02.2013 ታማኝ በየነ፡ ኦስሎ በተገኘበት፡ የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ፡ ምሽት ላይ የቀረበ፡