0
Posted December 11, 2012 in Amharic news
 
 

ደሮን ሲያታልሏት… በመጫኛ ጣሏት


በወያኔ/ኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረዉ የስልጣን ክፍፍል የፈጠረዉ የእርስ በርስ ሽኩቻ እያየለ መጥቶ ዛሬ አራቱ የእህአዴግ ድርጅቶች ካለመተማመናቸዉ የተነሳ እንኳን አገር መምራት ትናንሽ የፖሊሲ ዉስኔዎችንም በጋራ መወሰን አቅቷቸዋል። “የማይተማመን ባልንጄራ በየወንዙ ይማማላል” እንደሚባለዉ ኦህዴድ፤ ብአዴን፤ ደኢህዴግና ህወሀት ሁሉም ጠ/ሚኒስቴርና ሁሉም ምክትል ጠ/ሚኒስትር መሆን በመፈለጋቸዉ ቦታዉ አልበቃ ሲላቸዉ እራሳቸዉ የጻፉትን ህግመንግስት ደፍጥጠዉ ከሰሞኑ ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትር በመሾም አገራችን ኢትዮጵያን የሞኞች ድራማ መድረክ አድረገዋታል። ህዝብንና አገርን ያታለሉ እየመሳለቸዉ በተጨባጭ ግን እራሳቸዉን የሚያታልሉት የወያኔ ባለስልጣኖች እራሳቸዉ ጽፈዉ “ህገመንግስት” ብለዉ የሰየሙትን ከፍተኛዉን የአገሪቱን ህግ ጥሰዉ በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ አንድ አገር በአንድ ጠ/ሚኒስትርና በሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች እንዲመራ አድረገዋል።

ሰሞኑን በወያኔ መንደር የታየዉ በሹመት መንበሽበሽ ወያኔዎች ሊነግሩን እንሚፈልጉት ከልማትና ከእድገት ጋር ምንም ግንኙነት ዮዉም። ወያኔ ጠ/ሚኒስትር ከሾመ ከ3ወር በኋላ ሌሎቸ ሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች የሾመዉ በአራቱ አሻንጉሊት ድርጅቶች መካክል የኃ?ማሪያም ደሳለኝን ሹመት ተከትሎ የተፈጠረዉን ኩርፊያና የስልጣን ሽሚያ ለማርገብ አንደሆነ ከማንም የተሰወረ አይደለም። በተለይ በአገሪቱ ዉስጥ የሌለ የስልጣን መዋቅር ተፈልጎለት ምክትል ጠ/ሚኒስት ሆኖ የተሾመዉ የሙክታር ከድር ሹመት ስራ እንዲሰራበት ሳይሆን “ብዙሀኑን ያለቀፈ ዲሞክራሲ ድሞክራሲ አይደለም” በሚል መርህ ዙሪያ ተሰባስበዉ የዉስጥ ለዉስጥ ትግል የጀመሩትን የኦህዴድ አባላት ለማግባባት ነዉ። ሆኖም ትክክለኛዉን የነፃነት ትግል የጀመሩት የኦህዴድ አባላት እንደዚህ አይነቱን “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት” የሚሉትን የወያኔ የማጭበርበሪያ ሽፋን ተገንዝበዉ የኦሮሞ ህዝብ የማማባበያ ሳይሆን የትክክለኛ ስልጣን ባለቤት እስኪሆን ድረስ ትግላቸዉን ይቀጥላሉ የሚል የፀና እምነት አለን።

ወያኔ ከሰሞኑ ያደለዉ የስልጣን ራሺን  ኦህዴድ ዉስጥ የተነሳዉን  የስልጣን ይገባኛል  ጥያቄ ያፈነ ከመሰለው እጅግ በጣም ተሳስቷል። ይልቁንም ይህ የስልጣን ረሺን የሚያሳየዉ  ይህ ከእያንዳንዱ ድርጅት የተውጣጣዉ  የጠቅላይ ሚንስትርነት ድሪቶ መአት  ለሀገሪቱ ፈረስ እንሰራለን ብለው ግመል እየሰሩ መሆናቸውን ነዉ። የይህ በዚህ በኮሚቴ በተሰራ ግመል አይሉት ፈረስ ደግሞ ኦህዴድም ሆነ ሌሎቹ ወያኔ ሰራሽ ድርጅቶች አይታለሉም ብለን እናምናል።

ወያኔ ህግመንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ አገኘኋቸዉ እያለ ስንት ሰላማዊና ህግ አክባሪ ዜጎችን ወደጨለማ ቤት እንደወረወሯቸው የሚያዉቀዉ አባት፤እናት ወይም ልጅ የታሰረበት ቤተሰብ ብቻ ነዉ። ወያኔ ህግመንግስቱን የሚጠቀመዉ ተቃዋሚዎቹን ለማጥቃት ነዉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ እሱ እራሱ የጻፈዉን ህግመንግስት ሲያሰኘዉ ይለዉጠዋል፡ የደፈጥጠዋል ወይም ህገመንግስቱ የማይፈቅድለትን ነገር ያደርጋል እንጂ አንድም ቀን ህገመንግስቱን አክብሮ አያዉቅም። ለምሳሌ ባለፈዉ ሳምንት የሾማቸዉ ሁለት ምክትል ጠ/ሚነስትሮች በአገሪቱ ህግመንግስት የኒፈቅዳቸዉ ሹመቶች አይደሉም፤ ሆኖም ወያኔ እርሱን ከህግ በላይ አደርጎ ስለሚያይ ያሰኘዉን ይሾማል ያላሰኘዉን ደግሞ ስላልወደደዉ ብቻ ይሽረዋል።

ለዚህም ነው በወያኔ/ህወሃት ሀገራችን ኢትዮጵያ እየደረሰባት ያለውን ውርደትና እንግልት በመቃወም ስልጣን የህዝብ እንጅ የጥቂት አምባገነኖች  አይደለም በሚል ታጥቀን ይህ አካል ለህግ ተገዥ እንዲሆን ማስገደድ ወይም ማስወገድ አለብን የምንለው። አገራችን ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ስልጣንን ለብሄር ብሄረሰቦች በኮታ ማደል ሳይሆን እያንዳንዱ ዜጋና እያንዳንዱ ብሄረሰብ መብቱና ነጻነቱ ተከብሮ እራሱን በእራሱ እንዲያሰተዳድር ማድረግ ነዉ። ለዚህ ደግሞ ብቸናዉ መፍትሄ በህዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ስርዐት መገንባት ነዉ።

የኢትዮጵያን ህዝብ ለስልጣን አበቃነዉ እያሉ የሚፏልሉት የወያኔ ዘረኞች ዘሬ እነሱ እራሳቸዉ  ከፈጠሯቸዉ አሻንጉሊት ድርጅቶች ጋር የስልጣን ሸሚያ ዉስጥ የገቡት የአገሪቱን የጦር ኃይሎች፤ፖሊስ ሰራዊት፤ የደህንነትና የኤኮኖሚ ተቋሞች ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠሩ ነዉ። የወያኔ ፍላጎት አንድ ነዉ፤ እሱም ስልጣን አለ ቦታ ሁሉ ረግ ነዉመቆጣጠርና ሌላዉን ህዝብ ተከታይ ማድረግ ነዉ። ኦህዴድ፤ ብአዴንና ደኢህዴን እነሱ ብዙሃን ሆነዉ ሳለ ከሃያ አመት በላይ የወያኔ ተከታይ ሆነዉ ኖረዋል። ከአሁን በኋላ ግን ቁጥራቸዉንና የሚወክሉትን ህዝብ በሚመጠን መልኩ የፖለቲካ ስልጣን ካልጨበጡ ከወያኔ የኪራይ ቤት ወጥተዉ የራሳቸዉን ቤት መስራት አለባቸዉ።   ከአሁን በኋላ ለኦህዴድ፤ ለብአዴን፤ ለደኢህዴንና ለህወሀትም በሆን ልህልዉናቸዉ የሚበጃቸዉና ከታሪክ ተጠያቂነት የሚያድናቸዉ ከዚህ ሃያንድ አመት ሙሉ ከተጓዙበት አጥፊና አዉዳሚ መንገድ ወጥተዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ስርአት ገንብተዉ የበደሉትን ህዝብ መከስ ነዉ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!