0
Posted July 23, 2016 in Amharic news
 
 

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የአቋም መግለጫ ሐምሌ 15, 2008 ኖርዌይ !!


የጎንደር ሕዝብ እያደረገ ያለውን ፍትሃዊ ትግል ሙሉ በሙሉ እንደግፋለን !!

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የአቋም መግለጫ ሐምሌ 15, 2008 ኖርዌይ !!

ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ከተቋቋመበት መሰረታዊ ዓላማዎች አንዱና ዋነኛው በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ፍትሃዊና  የአንድ ዘር የበላይነት አገዛዝ  የሰፈነበትን አምባገነን ሥርዓት በማውገዝ  እንዲሁም በመታገል  ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን  ማለትም  የዜጎችን እኩልነት የተረጋገጠባት፣ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የተከበረባትና የተረጋገጠባት   የሕግ የበላይነት የሰፈነባት፣ እንዲሁም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በኩል አይን የሚታይባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጲያን ለመገንባት የሚደረገውን ህዝባዊ ትግል መደገፍና ብሎም በአጋርነት መቆም ነው፡፡

us-unity

እኛ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት አባላት የወያኔ መንግስት በመላው አገሪቱ ዜጎችን በማናለብኝነት ከትውልድ ቦታቸውና ከመኖሪያ አካባቢያቸው ማፈናቀልም ሆነ ይዞታቸውን በጠመንጃ አፈሙዝ መንጠቅ አንድን አገር አስተዳድራለሁ ያለን መንግስት ለሕዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል። ወያኔ ስልጣን በጠመንጃ ከያዘ ጀምሮ በመላው አማራ በጉራ ፈርዳ በጋምቤላ በኦሮሚያ ክልል በማስትር ፕላን ሰበብ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ ዜጎችን የመኖሪያ ቤታቸውን ከሀና ማርያም፣አቃቂ ቃሊቲ፣ላፍቶ ክፍለ ከተማና ሌሎችም አካባቢዎች ህዝብን ከይዞታቸው ማፈናቀል አሁን ደግም በጎንደር ወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን በጠመንጃ አፈሙዝ ለማፈን የሚደረገውን ትግል በማናለብኘነትና በአምባገነንነት የተወሰደና ሕገ ወጥ እርምጃ ነው

በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በጎንደር ከተማ  ከወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን ተንተርሶ  በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ  ላለፉት  ሃያ አምስት ዓመታት  የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ  ቀደም ሲል በቤጌምድር በኋላም በሰሜን ጎንደር በአማራነቱ ተከብሮ የኖረ ሕዝብ ስለሆነ ወደ ትግራይ ክልል መካለሉን በመቃወም ጥያቄዉን በአግባቡ ያቀረበ ቢሆንም ይህን በሰላማዊ መንገድ ላቀረበዉ ጥያቄ አንባገነኑ የወያኔ ጉጀሌ ቡድን የሕዝቡን ጥያቄ በሃይል ለማፈን የኮሚቴ አባላቱን ማሰርና ማፈን የቀጠለ ሲሆን ኮረኔል ደመቀ ዘዉዴ ለማሰር የሞከረዉን ሙከራ ተንተርሶ ሕዝብዊ ማዕበል/ቁጣ ተነስቷል። የሕዝብን ጥያቄ በሃይል ለማፈን እንደማይቻል ትላንት በኦሮሚያ የታየዉን ሕዝባዊ አመጽ ዛሬ በታሪካዊቷ ጎንደር ተደግሟል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት25 ዓመታት በአሸባሪውና በፋሽስቱ ወያኔ ቁጥጥር ሥር ከወድቀበትጌዘ አስቶ የፍዳ ዓመታትን እያሳለፈ ሲሆን  በእነዚህ ረጅም  የመከራ ዓመታት አንድም ቀን ወያኔን ከመታገል የተቆጠበበት ጊዜ ግን አልነበረም:: ወያኔ የማህበረሰቡን እሴት በቁጥጥር ስር ለማስገባት በአካሄደው አረመኔያዊ ድርጊት አሉ የሚባሉትን ማህበራዊ  እሴቶቻችንን  በሙሉ  ተራ  በተራ  ያፈራረሳቸዉና  በራሱ  አሻንጉልቶች በመተካት ፀረ ማህበረሰብ ዘመቻውን በሰፊው ገፍቶበታል። ይህ አንባገነን ሥርዓት  ኢትዮጵያ እንደሃገር ሕዝቧም እንደ ሕዝብ ቀድሞ  በነበረዉ  ሃገራዊ  ትስስር እንዳይቀጥል  ለእኩይ ዓላማዉ ሲል ብቻ  የሃገሪቷን ሕዝቦች  በዘርና በቋንቋ በመከፋፈል የሃገሪቷን ሕዝቦችን ሲያጣላና  እርስ በርሳቸዉ እንዳይተማመኑ በከፍተኛ ጥንቃቄ የሰራና በሃገሪቷ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰቦች ወይም ብሄረሰቦች  ከራሳቸው ዘር ውጭ ሌላውን ማመን የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ እየገቡ ለመሆናቸው በቅርቡ እየተፈፀሙ ያለው ድርጊት ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው። በጋራ ሁላችንም በሰውነታችን ብቻ ልንቀበላቸው የሚገቡ፣ ዘርን፤ ቋንቋንና ባህልን ተሻግረው ሊያስተሳስሩን የሚገቡ ጉዳዮቻችንን እያፈራረሳቸዉ ይገኛል።

የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በህዝብ ያልተወከለ አገሪቱን  የግዛት አንድነት ያላስጠበቀ፤ የሃገሪቷን አኩሪ የነፃነትና  የአንድነትን ታሪክ ገድል የካደና የናደ  እኩይ ቡድን ስለሆነ ይህ ቡድን ከህዝብ ጫንቃ ላይ ማስወገዱ አማራጭ የሌለዉ ወቅታዊና ሃገራዊ ግዴታ መሆኑን ዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት በጽኑ ያምናል።  በወልቃይት  ጠገዴ መሪዎች ላይ  ይህ አንባገነን  ታጣቂዎችን ከትግራይ ወደ ጎንደር በመላክ የኮሚቴ አባል የሆኑትን ኮለኔል ደመቀንና ሌሎችንም ለማፈን እንዲሁም ላለፉት ዓመታቶች  በወልቃይት ጠገዴ ማንነት ጥያቄ  አቅራቢዎች ላይ የጦር ሀይል፤ ደህንነትና ፖሊሶችን በማዝመት ጥያቄዉን ለማኮላሸት ቢሞክርም የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄዉን እንዲያቀርቡለት የመረጣቸዉ የኮሚቴዉ አባላቶች ለሚደርስባቸዉ ወከባና  እንግልት ሳይበገሩ የተጣለባቸውን አደራ ያለማወላወል በመጠበቅ ባካሄዱት አኩሪ የትግል ገድል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ታሪኩን በወርቅ ቀለም ፅፏል። ዘረኛው  ወያኔንና ተባባሪዎቹ የማይገባቸውና  እስከ ዛሬ ያልተረዱት የሕዝብ ፍላጎት ብሎም ቁጣንውን አሻፈረኝ አልገዛም ብሎ ማመጽ ወቅቱ ጠብቆ የሚመጣ ክስተት ነው። የወያኔ መንግስት ይሄንን ሕዝባዊ መነቃቃት ለማጥፈት በሌሎችም ላይ እንደሚያደርገው ሁሉ የተለያዮ ዘዴዎችን በመጠቀም ያላሰለሰ የሞት ሽረት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።አሁንም በተግባር እየፈፀመ ነው።

ዴሞክራሲያዊ ውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አምባገነኑ ህውሃት(ኢህአዴግ) በሰላማዊና በንፁሃን ዜጐች ላይ የወሰደውን ኃላፊነት የጐደለው እርምጃ አጥብቀን እያወገዝን የኢትዮጵያ ሕዝብ ልዩነቱን ወደ ጐን በመተው ይህንን ዘረኛ አምባገነን ስርዓት ለማስወገድ ከመቸውም ጊዜ በላይ ተባብሮ እንዲነሳ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ሊያሰሙ በወጡ ዜጎች ላይ የወሰደውን አረመኔያዊ እርምጃ በጥብቅ እያወገዘን የጎንደር ሕዝብ እያደረገ ያለውን ፍትሃዊ ትግል ሙሉ በሙሉ እንደግፋለን።ለተጀመረው የነጻነት ትግል ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አጋርነቱን ይገልጻል። 

ወያኔ በማስወገድ የሃገራችንን አንድነትና ዳር ድንበር እናስከብር!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!!

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ !!!!