0
Posted April 24, 2015 in News
 
 

የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ለኢትዮጲያና ለሕዝቧ ክብር ስለማይመጥን ይወገድ!!!!


ተስፋዬ ዘነበ (ስታቫንገር)

የረጅም ጊዜ የነፃነት ታሪካችን በመቻቻልና በመከባበር አብሮ የኖረው ህብረታችን፣ ለሃገራችን  ነፃነት ያደረግነው ተጋድሎ፣ ኢትዮጲያን እንደ ታላቅ  ሉአላዊት ሃገር በጠንካራ መሰረት ላይ ያቆማት ምህተ አመታትን ያስቆጥረ ጠንካራ ማንነታችን ነው፡፡ በዚህ ባለንበት ሃያ አንደኛው ክ/ዘመን የኛን አባቶች የነፃነት ተጋድሎ የነፃነት ታሪክ ተምሳሌት አርገው በኛ ፈር ቀዳጅነት እንደ ሃገር ሉአላዊነታቸውን የተቀዳጁ ሃገራት የተቀዳጁትን ሃገራዊ ክብር በተግባር ሲመሰክሩ፣ እኛ  ለነፃነት የመጀመሪያዎቹ፣ እኛ ቀደምት የነፃነት ፋና ወጊዎቹ፣ እኛ ስለ ሌሎች በባእዳን ተፅእኖ ስር ለወደቁ የአፍሪካ ሃገራት ተሟጋቾች፣ እኛ ስለ ነፃነት ትግል አስተማሪዎችና ለጋሾች፣ መከታዎች፡ ክብራችንን የሚያስጠብቅ የቀደመ ማንነታችንን የሚያስጠብቅ፣ ለሃገራችን ሉአላዊነት የሚታገል፣ ታፍሮና ተከብሮ ለኖረ ኢትዮጲያዊ ማንነታችን ቀናኢ ሆኖ የሚሟግርትልና በአንድ ኢትዮጲያ ጥላ ስር የሚሰበስበን የኛ የሃገራችን የሕዝባችን የምንለው ለዚች ታላቅ ሃገር የሚመጥን፣ ለሃገርና ለሕዝብ ታማኝ የሆነ እንዲውም ሃገሩና ሕዝብን የሚወድ አስተዳደር(ስርዓት) አጥተን ለመስማትም ሆነ ለማየት የሚዘገንን ግፍና ሰቆቃ በውስጥም በውጪም ስንቀበል እንሆ ዘመናት ተቆጠሩ፡፡

በተለይ ለዚች ታላቅ ሃገርና ሕዝብ ክብር የማይመጥን፣ እንዲሁም ለዘመናት ውድቀታችንን ሲሸርቡልን ከኖሩ የተለያዩ ሃይሎች ባልተናነሰ ምንም አይነት የሃገርና የሕዝብ ፍቅር የሌላቸው ከአንድነት ይልቅ መበታተንን፣ ከክብር ይልቅ ውርደትንና መሸማቀቅን፣ ከብሔራዊ ሃገራዊ ስሜት ይልቅ ጠባብ ቤሔርተኝነትን፣ ከአብሮነት ይልቅ ጥላቻንና መከፋፈልን ለዚህ ሃይማኖትና ብሔር ሳይለየው ለዘመናት በፍቅር ለኖረ ታላቅ ሕዝብ በግድ እየጋቱ የራሳቸውን የጫካ ስርዓት የሚጭኑበት የምን ግዜም የሃገርና የሕዝብ ጠላት የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ለመሆኑ ተግባሩ የሚመሰክረው ስለሆነ እማኝ አያስፈልገውም፡፡

ሃገራችን አሁን ለደረሰችበት ቤሔራዊ ውርደት ድህነትና በዜጎች ላይ ለሚደርሰው ዘግናኝና ከሰው ልጅ አህምሮ በላይ ለሆነው ስቆቃ ያበቃን በጉያችን ታቅፈን የግፍ ቀንበሩ ተሽካሚ ያደረገን  ዘረኛው የትግራይ ወያኔ አገዛዝ ነው፡፡

ከግዜ ወደ ግዜ አላባራ ብሎ ይልቁንም አስከፊነቱ ከእለት ወደ እለት እየጨመረ የመጣው በሃገራችን በሰላም ሰርቶ የመኖር እንዲሁም እንደ ሰብአዊ ፍጡር በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በሃገራችን የመኖር ዋስትና በማጣት እንደ ጨው ዘር ተበትነው የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ በየግዜ የሚደርሰው እልቂት የአለም ሕዝብ መነጋገሪያና መዘባበቻ የሆነው በታሪካችን በዚህ ለሰው ክብር ደንታ በሌለው የወያኔ ዘረኛ ቡድን መዳፍ ላይ ሃገረችን ከወደቀች በኋላ ነው፡፡ ለራሳቸው ጥቅም  የሕዝብና የሃገር ሃብት መዘብረው ከደለቡበት ወንበራቸው ውጪ ለምንም ደንታ የሌላቸው ገዥዎቻችን ይህንን ታላቅ ሃገርና ሕዝብ የመምራት ብቃትም ሆነ ተፈጥሯዊ ባህሪ እንደሌላቸው በተደጋጋሚ በዜጎች ላይ ለሚደርሰው ሰቆቃና አደጋ የሚሰጡት ከሰብአዊ ፍጡር የማይጠበቅ እጅግ የዘቀጠ መግለጫ ፍንትው አርጎ ያሳየናል፡፡

ይህ ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ ለዝች ታላቅ ሃገር አይመጥንም ስንል – ሃገራዊ ቅርሳችንን በማፍረስና ጥንታዊ ታሪካዊ ዳናችንን በማጥፋት ከገዳም እስከ መስኪድ የእምነት ተቋማትን ሁሉ ሲያፈርስና የእምነት አባቶችን ሲስርና ሲያሳድድ ማየቱ  የሚያረጋግጠው ስርዓቱ የቀደመ ክብራችንን ማስጠበቅ አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን አለመፈለጉም ከሚያራምዳቸው ተግባራት በግልጽ የሚታይ ነው፡፡ የሃገሪቱ አንጡረ ሃብት ከላይ እስከ ታች በሙሉ በመቆጣጠርና በመመዝበር ለዜጎች ምቹ እንዳትሆ በማድረግ አሁን ለተፈጠረው ብሔራዊ ውርደትም ሆነ የስብእና መዋዠቅ ተጠያቂው ሃገራዊ ፍቅር አልባው አገዛዝ ነው፡፡ በተጨማሪም አገዛዙ ከሚያራምደው ከፋፍለህ ግዛ መርሁ አንጻር ለዘመናት በአንድነት የኖረው ቤሔራዊ አንድነታችን የሚያመውና በጥልቅ የሚጠላው ስለሆነ እንደምናየው ይህቺን ሃገር ወደ ውድቀት የሚውሰድ እንጂ በአግባቡ የመምራት አቅምም ፍላጎትም የለውም፡፡

ይህው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ይቺን ሃገር የመምራት አቅም የለውም ስንል- አገዛዙ እራሱን የባህዳን ተገዢ ያደረገና በሕዝብ ስም በለመነው እርዳታ ስለሚታዳደር እንደ አንድ ሃገር   በተለይ በውጪ ግንኙነቱ በራሱ የመወሰን አቅም ስለሌለው (ባለመኖሩ) ብዙ ሃገራዊ ጥቅሞችን ለገዥዎቹ አሳልፎ ሲሰጥ ኖሯል እየሰጠም ነው፡፡ በተጨማሪም ጥገኝነቱ በራስ መተማመንን ስለሚያሳጣው በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ በዜጎቻችን ላይ ለተፈጸመው ፍጹም ኢሰብአዊ ድርጊት እንደ ሌሎቹ አፍሪካዊ ሃገራት ማድረግ የሚችለውን ከማድረግ ይልቅ ይህንን የመጠቃትና የመደፈር ሃገራዊ ጉዳይ በማሳነስ የገለጹበት መንገድ ለዚች ታላቅ ሃገርና ሕዝብ የማይመጥን ፍጽም የወረደ በአገዛዝ ለመሆኑ ማሳያ ነው፡፡

ይህ ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ ለዝች ታላቅ ሃገር አይመጥንም ስንል -አገዛዙ በስልጣን በቆየበት ሁለት አስርተ አመታት እንድ ሃገርም እንደ ሕዝብም እጅግ የተዋረድንበት እጅግ የተናቅንበት ከመሆኑም ባለፈ የወያኔ አገዛዝ በማህበራዊ፣ ኤኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ በሆኑ ጉዳዮች በራሱ መንገድ እንደ ቦይ ውሃ እንድንፈስ እግር ከወርች አስሮ ቤሔራዊ አንድነታችንን ለመበተን ቀን ከሌት የባከነበት ግዜ ነው፡፡ አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጲያን ለማቆየት የማይመጥናት የትግሬ ወያኔ ቡድን ግዜ ሳይሰጠው መወገድ ይኖርበታል፡፡

ይህ እኩይ ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ በፍጹም ለኢትዮጲያና ለህዝቧ አይመጥንም ስንል- አገዛዙ ሃገሪቷን በሃይል ከተቆጣጠረ ጀምሮ የራሱ ተላላኪዎች ጭምር በተሰማሩበት የሰወች ዝውውር ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ የደሃ ልጆችን በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራትና አረብ ሃገራት በመላክ ፍፅም በማይመች ሁኔታ ሕይወታቸውን እንዲገፉ ዳርጓቸዋል እራስን ለመቻልና ቤተሰብ ለመርዳት ለገርድና የተጋዙት ብሎም የመረረ ሕይወት በመግፋት በአሰሪዎቻቸው የተደፈሩ፣ በቢላ የሚበለቱት፣ የፈላ ውሃ የሚደፋባቸው፣ ተስፋ በመቁረጥም በገመድና ከፎቅ በመከስከስ እራሳቸውን የሚያጠፉ አለሁ ባይ ስለ መብታቸው ተከራካሪ፣ ጥበቃ የሚያደርግላቸው መንግስት የሌላቸው በአገዛዙ የተረሱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችን የዚሁ ስርዓት እድሜ ያላቸው ዜጎች ናቸው፡፡

ጎጠኛው የወያኔ አገዛዝ ታላቅ ታሪክና ክብር ላላት ሃገር አይመጥንም ስንል- ገዢዎቻችን ነጋ ጠባ ሁለት አሃዝ አድገናል እያሉ የሚወተውቱት ጠብ ያላለለት ምስኪን ሕዝብ በአብዛኛው ወጣቱ አገዛዙ ሃገራችንን በሃይል ከያዘ በኋላ የተፈጠሩ እናም በስርዓቱ ብልሹ አስተዳደር እንደ ዜጋ የነሱ የሆነውን ሁሉ በዘረኛው አገዛዝና በአገዛዙ አጋፋሪዎች የተነጠቁ ሕይወታቸውን ለማቆየትና ችግረኛ ቤተሰባቸውን ለመደጎም ከፊታቸው ሞት እየጠበቃቸው ባህርና በረሃ አቋርጠው  ለጨካኞቹ የደቡብ አፍሪካ ዙሉዎች ገጀራና እሳት እንድሁም ከላይም ከታች  የጥይት ሃረር በሚያፏጭበት የመን ለሞትና ለስቃይ  የተዳረጉት፣ በሊቢያ በረሃ አይ ኤስ ኤስ   በተባለው ሴጣናዊ ቡድን እጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ በግፍ የተቀሉት  ወገኖቻችን ለዚህ የተዳረጉት ሃገራችን ላይ ባስቀመጥነው  ጭራቅ የወያኔ አገዛዝ ተገፍተው እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው፡፡

በተጨማሪም አገዛዙ አዋርዶናል አይመጥነንም ስንል -ህብረተስቡን የማይወጣበት የድህነት አዘቅት ውስጥ የከተተው ይህው ስርዓት በራሱ እድሜ የሚለኩ ወጣት ሴቶች በባህላችን ነውረኛ ተግባር የሆነውን ገላን ሸጦ የመተዳደር ፀያፍ ተግባር ከመሸታ ቤት አልፎ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ሳይቀር ያለ እፍረት መከወኑ አገዛዙ በቆይታው ያመጣብን የስብእና መላሸቅ ውጤት መሆኑ ይታያል፡፡

እንግዲህ ከሞላ ጎደል ወያኔ ለቀደመ ክብራችን የማይመጥን የማፍያ ቡድን መሆኑን ለማሳየት ተሞክሯል ስለሆነም አንገታችንን የደፋንበት ያዘንበትና እንደ ሃገር የደረሰብን ክብረ ነክ  ድርጊት እንዲሁም ከዳር እስከ ዳር  ማቅ ያለበሰንና በእንባ ያራጨን መራራ ሀዘን ዳግም በዝች ሃገርና ህዝብ ላይ እንዳይከሰት ለሃገር ብሎም ለሉአላዊ ነፃነት ግድ የሚለው እንደ ቀደምት አባቶቻችን ተከብሮ የሚያስከብረን ኢትዮጲያዊ የሆነ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሊኖረን ግድ ይላል!!! ይህ የሚሆነው የወያኔ ዘረኛ ብድን ያደረሰብንንና እያደረሰብን ያለውን ተነግሮ የማያልቅ በደልና ግፍ መላልሰን በማመንዠግ ሳይሆን አገዛዙን ለማስወገድ በሚደረገው ሁለገብ ትግል ባመቸን መልኩ በመሳተፍ የወያኔን ግባ ከመሬት ስናፋጥን ብቻ ነው፡፡ ለህዝብና ለሃገር ያልታመነ አገዛዝ መሰረት የለውም፡፡ ውበታችንና ጥንካሬያችን አንድነታችን ነው!!  በሄድንበትና በተሰደድንባቸው ሃገራት ቢሆን እየደረሰብን ያለው በደልና እንግልት ብሎም ግድያ ይህው የወያኔ አገዛዝ እንዲጠፋ የሚፈልገው ኢትዮጲያዊነት ስማችን ፣ ማንነታችን ሆኖ እስከሞት ሸኝቶናል፡፡

ዘላለማዊ ክብር በሊቢያ በግፍ ለተቀሉ ኢትዮጲያዊያን ሰማህታት!!!!!

ኢትዮጲያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!!!

Ftih_lrwegen