0
Posted May 25, 2014 in Amharic news
 
 

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ በርገን ቅርንጫፍ የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ያደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በመቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረገየዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ በርገን ቅርንጫፍ የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በመቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በግንቦት 23. 2014 ዓ.ም በበርገን ያካሄደ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዮንቨርስቲዎች በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮሚያ ልዮ ዞን ከተሞች የጋራ ማስተር ፕላን በሚል ገዥው መንግስት ያወጣውን እቅድ በመቃወም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ በወጡ ንጹሀን ተማሪዎች ላይ ዘረኛው የወያኔ መንግስት ከዚህ በፊት በ1997 ዓ.ም በወገኖቻችንን ላይ እንዳደረገው አልሞተኩዋሾችን በማሰማራት ወገኖቻችንን ግንባርና ደረታቸውን በጥይት በመበርቀስ የነገ ተስፋዎቻችንን በወጡበት እንዲቀሩ አድርጉዋል ::
ይህ የወገኖቻችንን ስቃይና ሞት ያስቆጣው በበርገንና ዙሪያዋ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የተቃውሞ ድምጹን ለማሰማት ከተባለው ሰዓት ቀደም ብሎ ነበር የኢትዮጵያን ባንዲራ፣ የሟች ወገኖችችን ምስል ያለበት መፈክር እና በትልቅ ጨርቅ ላይ የተፃፈ ግድያውን የሚያወግዝ ፅሁፍ አንግቦ በቦታው ለይ የተገኘው :
ለተፈጠረው ቀውስ መነሻው ማስተር ፕላኑ ይሁን እንጂ ወያኔ በህዝባችን ላይ ላለፉት 23 ዓመታት ይከተለው የነበረው የዘር ፖሊሲ ፣ የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣የመልካም አስተዳደር እጦት፣የሙስና መስፋፋት ፣ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ የበይ ተመልካች መሆናቸው የፈጠረው እምቅ ብሶት ድምር ውጤት እንደሆንም መገንዘብ ይቻላል::
አቶ አንተነህ አማረ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ በርገን ቅርንጫፍ ዋና ሰብሳቢ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ካስተላለፈ በኋላ ገዥው መንግስት በቅርቡ በወገኖቻችን ለይ እየፈፀመ ያለውን ዘግናኝ ግድያ ፣እስር እና እንግልት የሚያሳይ ዘርዘር ያለ ፅሁፍ ያቀረበ ሲሆን :በማስከተልም አቶ ዳዊት እያዩ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ በርገን ቅርንጫፍ የህዝብ ግኑኘነት ኋላፊ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ የአቋም መግለጫ አቅርቧል: በመጨረሻም አቶ ማርቆስ ዐብይ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ በርገን ቅርንጫፍ ዋና ፀሀፊ የሰልፉን ዋና መልእክት የእንግሊዝኛውን ቅጂ ለሰልፈኛው ያቀረበ ሲሆን :
በመርሀግብሩ መሰረት ሰልፈኛው ድምጹን ከፍ አድርጎ ግድያውን የሚያወግዙ መፈክሮች በማሰማት ጉዞውን ወደ በርገን ማዘጋጃ አድርጓል :በእለቱ ይሰሙ ከነበሩት መፈክሮች መካከል ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ፣ የንጹሀን ደም በከንቱ መፍሰስ የለበትም፣ኖርዌ አንባገነንን አተደግፊ፣ ነፃነት እንፈልጋለን የሚሉት የገኙበታል: ይህንን የተቃውሞ ሰልፍ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት ሰልፎች ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ከዚህ ቀደም በወያኔ ሴራ የጎሪጥ ይተያዩ የነበሩ ወገኖችን ልዩነቶቻቸውን ወደጎን በመተው ለጋራ ችግራቸው በጋራ መቆም መቻላቸው ነው::
በመጨረሻም ሰልፈኛው በጋለ ስሜትና ቁጭት በመዘጋጃ ቤቱ በር ላይ መፈክሮቹን ያሰማ ሲሆን በእለቱ ተዘጋጅቶ የነበረውን የሰለፉን መልእክት የያዘውን ደብዳቤ ለሀገረ ገዢው ተወካይ በማሰረከብ ሰልፉ ተጠናቋል::
ይህንን ትእይንት በቦታው ላይ በመገኘት በቀጥታ ስርጭት ታዋቂዋ የኢሳት ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን የዘገበችው ሲሆን የኖርዌ ጋዜጠኞችም በቦታው ላይ በመገኘት ለሰልፈኛው ቃለመጠይቅ አድርገዋል::
ይህ ዝግጅት የተሳካ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያደረጉ የ DCESON በርገን ቅርንጫፍ ጽ∕ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም የዘወትር ተባባሪያችን የቶም ሰቱዲዮ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ ቶማሰ አለባቸው ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል::

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ በርገን ቅርንጫፍ/ ማርቆስ ዐብይ /