1
Posted May 25, 2014 in Amharic news
 
 

የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞች ቀን ሜይ 3/2014 በስታቫንገር ኖርዌይ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የስታቫንገር ቅርንጫፍ አዘጋጅነት ውይይት ተደረገየቀኑ ፕሮግራም በ17᎓30 በድርጅቱ አባል አማካኝነት የቀኑን መርሃ ግብር በማስተዋወቅ የተከፈተ ሲሆን በዚህም መሰረት
• በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን አጠቃላይ የእስረኞችን አያያዝ እና የአምባገነኑን የወያኔ ስርአት ምክንያንያት በማብራራት
• በአንድነት ለዲሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ እና በሰማያዊ ፓርቲ ላይ እየደረሰባቸው ያለው እስራት እና መከራ በተጨማሪ ሰሞኑን ከእየቤታቸው የታፈኑትን ወጣት ጦማሪያን አሳዛኝ ሁኔታ በመጥቀስ
• በወያኔ አገዛዝ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ የደረሱትን በደሎች በሰፊው በማስረዳት ንግግራቸውን ጨርሰዋል᎓᎓

የዲሞክሪሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት የስታቫንገር ቅርንጫፍ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አብዩ ጌታቸው DCESON በስታቫንገር ከተማ ለማቁዋቋም ለምን እንደአስፈለገና እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴ እና ስለድርጅቱ አላማ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሲሰጡ DCESON የኢትዮጵያ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ቀን በእስታቫንገር ለምን ማዘጋጀት እንዳስፈለገና በኢትዮጵያ ሐገራችን ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ያስቀመጣቸውን እቅዶችን በሰፊው ገልጸዋል᎓᎓ DCESON እንዴት ባለ መንገድ መርዳት እንዳለብንና እና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ እንዴት ለመስራት እንዳሰበና እንዴት እየሰራ እንደሆነ በማስረዳት አብራርተው ገልጸዋል እንዲሁም ድርጅቱ በኢትዮጵያ የሚገኘውን አምባገነን መንግስት እንዴት ባለ መንገድ መታገል እንዳለብን ስለቀየሰው መንገድ ማብራሪያ ሰጥተው በመፍትሄው ዙሪያ የሁላችንም ተባባሪነት ወሷኝ መሆኑን በመግለፅ ንግግራቸውን ጨርሰዋል ᎓᎓

እንዲሁም የተለያዩ እንግዶች በዝግጅቱ ላይ ተየጋበዙ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣና እንግልት በሰፊው በእንግዶቹ ዓማካኝነት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን እደዚሁም በኢትዮጵያ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በተመለከተ አጭር ግጥም የቀረበ ሲሆን በወቅቱ ከተነሱት ርእሶች መካከልም፥

  1. በኢትዮጵያ ያሉ እስረኞ እንዴት በተለያየ እስር ቤት ላይ እንዳሉ ለያይተው ለማሳየት የሞከሩ ሲሆን በጨለማ ቤት ለብቻቸው የታሰሩ፥ በብዛት በአንድ ቦታ የታጎሩ፥ በተወሰነ አካባቢ እና ቦታ ከሌሎች እስረኞች ተለይተው የተቀመጡ በማለት ያብራሩ ሲሆን በሰብአዊነትና በፖለቲካ አመለካከት ያለውን ልዩነት በጥልቅ አብራርተው በተጨማሪም ኢትዮጵያ ሃገራችን የሰው ልጅ ሰብአዊ መብት እንዲከበር በተደረገው ጥረት ላይ የነበራት አስተዋፅኦ አስታውሰው አስረድተዋል᎓᎓ በመጨረሻም የፖለቲካ ወገኝትነት ነፃ የሆኑ ተቋማትና ማህበራት ለዲሞክርሲያዊ ግንባታ ወሳኝ መሆናቸውን
  2. Prisoners of concunese የሚል ዘጋቢ ፊልም ቀርቦ በህሊና እና በፖለቲካ እስረኛ መካከል ያለውን ልዩነት በጥልቀትና በምሳሌ ማብራሪያ የተሰጠበት ሲሆን ከሃገር ውጭ የምንኖረው ኢትዮጵያኖች በፖለቲካው ላይ ሊኖረን ስለሚገባ ድርሻና ግንዛቤ
  3. በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ያተኮረ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን የህይወት ታሪክ እና ያሳለፈውን መከራ እና ያስገኛቸውን ድሎች እና በጋዘጠኛ እና መምህር ርዕዮት አለሙ ዙሪያ ላይ የደረሰውንና ሚደርስባትን እንግልት እና ስቃይ በተጨማሪም በዚህ መሰናክል ውስጥም ያስመዘገበችውን ድል እና ሽልማቶች የተገለፀ ሲሆን ሌላው ለምን እና እንዴት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያን እስረኞች አገራችን እንዳፈራችና እየተከሰተ ያለው ችግር አሳሳቢነትን በዝርዝር የተብራራ ሲሆን

በተነሱት በርካታ ነጥቦች ላይም ከስብሰባው ታዳሚዎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ባጠቃላይ ስብሰባው የተለያዩ ገንቢ አስተያየቶችን ተንፀባርቋል᎓᎓ በመጨረሻም ለዚህ ፕሮግራም መሳካት የተባበሩትን አቶ ዳንኤል ሙሉ በፊልም እና ፎቶ ማንሳት አቶ አብዶ የሱፍ(በስታቫንገር የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት የስታቫንገር ቅርንጫፍ ምክትል ሰብሳቢን እና እንዲሁም አቶ አቤል መኮንን ለዘገባው ላደረጋችሁት ጥሩ ስራ ከልብ እናመሰግናለን᎓᎓

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በስታቫንገር ቅርንጫፍ