0
Posted April 10, 2014 in Featured
 
 

ኢሳት እና ኢቲቪ


የአገዛዙ አፈናና የኢሳት ተፅህኖ

OLYMPUS DIGITAL CAMERA

ዮናስ ኤልያስ (ኦስሎ ኖርዌይ)

መጋቢት 26 2006 ዘጠና ሚሊዬን ህዝብ እንዳለ በሚነገርላት ኢትዪጵያ የተለያዩ የፖለቲካ ፤ የሃይማኖት፤ የዘር እና ሌሎችም አመለካከቶች የሚኒፀባረቁባት(የሚስተናገዱባት) ሃገር መሆንዋ እርግጥ ነው። ታዲያ እነዚህን ሁሉ አመለካከቶች የሚያስተናግዱ የሚዲያ ተቋማት መኖራቸው የሚጠበቅ ጉዳይ ነው ቢሆንም የተለያዪ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የግል የሚዲያ ተቋማት እንዲኖሩ ማበረታታት ከተቻለ ደግሞ በተለያየ መንገድ መደገፍ ማገዝ አገሪቷን ከሚያስተዳድረው አካል የሚጠበቅ ነበር፤ ማለትግን ነው ማለት  አይሆምንና አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው አገዛዝ ባህሪ በመነሳት የማይጠበቅ ነገር ሆኖ ሳይሆን ይህንን በዝምታ መመልከት ማለት ደግሞ ይህ በእንዲህ እንዲቀጥል መፍቀድ ከመሆኑም ባሻገር

 

download (1)download

ኢ ሳት/ESAT                                                                                                                         ኢቲቪ/ETV

    

   ሃገሪቷን ከመምራት ይልቅ የሚያስመርራት መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖር የፈቀደው የሚዲያ ተቋም ኢቲቪና በአምሳያው የተጠፈጠፉ የመገናኛ (አንዳንዶቹ መናኛ) ብዙኌን ይሏቸዋል ናቸው በኢቲቪና የኢትዪጵያ ሬዲዮ በ አዲስ ዘመንና በአዲስ ልሳን በሬድዮ ፋናና በኤፍ ኤሞቹ መካከል የሰዎች ካልሆነ የሚያቀርቡት የዜናም ሆነ የመረጃ ልዩነት የለም ስለሆነም ስለ ኢቲቪ ስናወራ በአምሳያው ስለተጠፈጠፉት የሚዲያ ተቋማት እያወራን መሆኑ መቼም ያግባባናል።

እንደ ኢቲቪ አይነት መንቻካ የሚለው ቃል ብቻ የማይገልፀው ደባሪ የቴሌቭዥን ጣቢያ  ሌላ ቦታ ካለ ያለው የኪም ዮንግ ዑን ሃገር ሰሜን ኮርያ ብቻ ነው «ወይ አያምር ወይ አያፍር» የሚባለው ኢቲቪ በመንቻካዎቹና በደረቆቹ ልማታዊ (ሌማታዊ)  ጋዜጠኞች በመታገዝ እንኳን ሌላው ሰው ቀርቶ እራሳቸውም የማያምኑበትን ፕሮፓጋንዳ ወገባቸው እስኪጎብጥ ድምጻቸው እስኪቀጥን  ድረስ ያለማቌረጥና ያለመታከት ያስተላልፋሉ አንዳንዴ አላማቸው ማሳመን ሳይሆን ማታከትና ሰው ድክም ሲለው ይሁንላቸው ብሎ ይቀበለናል በሚል መልኩ የሚቀርብ ነው የሚመስለው፤ የሚገርመው ነገር አመቱን ሙሉ ያደከሙበትን  የቴሌቭዥን ግብር ብለው መጠየቃቸው ነው «አመታዊውን የቴሌቭዥን ግብር ከፍለዋል» የሚል ማስታወቂያ ሲያስነግሩ ያለምንም ይሉኝታ መሆኑ ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ነው፤ መሆን የነበረበት ግን ኢቲቪን ያየና  የሰማ ክፋያ ይገባው ነበር ልክ ገዢው ፓርቲ ለሰልፍና ለስብሰባ አበል እንደሚከፍለው  ማለት ነው የሆነው ሆኖ ይሄ ሁሉ ነገር የሚደረገው  በግብር ከፋዪ ወጪ መሆኑ ማስገረሙ ካቆመ ብዙ ግዜ እየሆነ ነው የተለያዪ አመለካከቶችን ሊያስተናግድ ይገባ የነበረ ጣቢያ የገዢው ፓርቲ ልሳን ከሆነ 23 አመታት እየሆነው ነው  እንደ « ድምፅ ወያኔ » ስሙን « ምስለ ወያኔ » ብሎ አልሰየመም ወይ አልቀየረም እንጂ በተግባር ግን የወያኔ ቴሌቭዥን ጣቢያ መሆኑን የማያምን ኢቲቪን አይቶ የማያውቅ ወይም የአገዛዙ ደጋፊ ወይ ተደጋፊ መሆኑ እውነት ነው። አገዛዙ በራሱ እንደማይተማመን  ሌላው ማሳያ ሊሆን የሚችለው ጉዳይ ኢቲቪን እና ኢቲቪን የመሳሰሉ  በርካታ የሚዲያ ተቋማት በመቶ ምናምን ሚሊዬን ብር በጀት በብዙ ሺህ በሚገመቱ ሰራተኞች እያንቀሳቀሰ ሌሎች አማራጭ የሚዲያ ተቋማት እንዲኖሩ ድፍረት የሌለው መሆኑ ሲታይ ነው።

ለነገሩ የቴሌቭዝን ጣቢያ ቀርቶ በጥቂት ሰዎች የሚንቀሳቀሱ የህትመት ውጤቶችን እንኳን እንዲኖሩ የማይፈቅድ አፋኝ ስርአት ነው እንግዲህ በዚህ ሁሉ መሃል ነው    ኢሳት ብቅ ያለው የኢሳት ወደ መረጃ መድረኩ መምጣት ለአገዛዙ እራስ ምታት መረጃ ለተጠማው ህብረተሰብ ደስታን የፈጠረ መሆኑ ሃቅ ነው፤ ኢሳት ነፃና ገለልተኛ የሚዲያ ተቋም ነው ብሎ የሚያምን በርካታ የህዝብ ነው በአንፃሩም ኢሳት አማራጭ ነው የሚሉም እንዲሁም በርካቶች ናቸው አንዳንዶች ደግሞ ኢሳት የተቃዋሚዎች ልሳን ነው ብለው የሚሞግቱ አሉ እነዚህን ክርክሮች ለተከራከራካሪዎቹ እንተውና ኢሳት ነፃም ሆነ አማራጭ ወይም የተቃዋሚ ልሳን ቢያንስ ኢቲቪን አይደለም የተቃዋሚ ልሳን ቢሆን እንኳን ለውጥ አያመጣም ተቋዋሚ ልሳን አያስፈልገውም ያለው ማን ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አገዛዝ ሃገሪቷ ውስጥ ያለውን የሚዲያ  ያለምንም ገደብ እየፈነጨበት ህዝቡና ተቃዋሚው መተንፈሻ ባጡበት ሰአት የህዝቡና የተቃዋሚው ልሳን ከሆነ ያለማጋነን ኢሳት በትክክለኛ መንገድ ላይ ነው ያለው እላለሁ።    ኢሳት የሚተዳደረው ሞልቶ በተረፈው የሃገሪቱን ሃብት እንደፈለገው በሚያደርገው መንግስት አይደለም ይልቁንም በውጪ ካለው ኢትዮጵያዊ 10 እና 20 ዶላር እየተሰበሰበ ነው እንደፈለገ የሚቀጥረው ወይ የሚያባርረው የሰው ሃይል ሊያገኝ በሚችልበት ሁኔታ ውስጥም አይደለም ስለዚህ የኢሳት ድክመትና ጥንካሬውም  እየሰጠ ያለው አገልግሎትም መታየት ያለበት ካለበት ሁኔታ አንፃር ነው።

በውጪ ሃገራቱ ያለው ኢትዮጵያዊ በፍቃደኝነት ማንም ሳያስገድደው ለኢሳት ድጋፉን በሚገርም ሁኔታ እየሰጠ ነው ይህም ህብረተሰቡ ለነፃ ሚዲያ ያለውን ድጋፍና ፍላጎት ያሳየበት መንገድ ነው ኢሳት የሚንቀሳቀሰው ፍቃደኛ በሆኑ ግለሰቦች ትብብር መሆኑ ነጻ ለመሆኑ አንድ ማሳያ ነው ለመሆኑ ማን ነው ለኢቲቪ በፍቃደኝነት ቀይዋን ሳንቲብ  ሊያዋጣ የሚችለው ኢሳት ከኢትዮጵያውያን በገዝው መንግስት የተደበቁ ወይም እንዲነገሩ ያልተፈለጉ ዜናዎችንና መረጃዎችን ለህዝብ ማቅረቡ  ወይም እያቀረበ መሆኑ ግልጽ ነው ይሄም በመሆኑ ኢሳትን ለማፈን እራሱ ኢሳት ከሚተዳደርበት በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ከፍተኛ ባጀትና የሰው ሃይል  አገዛዙ መድቦ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይደርስ ያለማቋረጥ ለማፈን የሚንቀሳቀሰው ኢሳት ባይኖር ሊሰሙ የማይችሉ የአገዛዙ ስንክሳሮች የወጡትም በዚሁ በኢሳት በመሆኑ ነው የሩቆቹን ትተን የቅርቦቹን ብናይ እንኳን አለምነህ የተባለው የብአዴን ባለስልጣን እመራዋለው በሚለው ህዝብ ላይ የተናገረውን አፀያፉና አሳፋሪ  ንግግርና በዚህም የተነሳ በባህርዳርለተደረገው ብዙ ሺህ ህዝብ ለተሳተፈበት ሰልፍና የፖለቲካ መነቃቃት እንዲሁም አገዛዙ ከሱዳን ጋር አድርጎታል ስለተባለው  ሚስጥራዊ ስምምነት ለህዝብ ጆሮ እንዲደርስ ያደረገው ይሄው ኢሳት መሆ ኑ ሲታይ ጣቢያው  የመረጃውን ክፍተት ለመሙላት የሚያደረገውን ጥረት ከተቻለ ማገዝ ካልተቻለ ደግሞ አለመገዝገዝ ከጤነኛ ሰው የሚጠበቅ ተግባር ነው።

በአለም ላይ ስለ ነፃ የሚዲያ ተቋማት የተለያዩ የንድፈ ሃሳብ ክርክሮች ቢኖሩም በአለም ላይ ነፃ ሚዲያ የለም እስለማለት ደረጃ የደረሱ  ወይም የሚደርሱ ክርክሮችና ተከራካሪዎች ቢኖሩም ዲምክራሲና ነፃነት ባለባቸው ሃገሮች ውስጥ ነፃ ሚዲያዎች ባይኖሩ እንኳን ህብረተሰቡ የተለያዪ አማራጭ መረጃዎችን ከተለያዩ  ሚዲያዎች ስለሚያገኙ ወይም ማግኘት ስለሚችሉ የጉዳዩ አሳሳቢነት ብዙም አይደለም እንደ ኢትዮጵያ አይነት ባሉ ሃገሮች ውስጥ ግን ባለው ፍፁም አንባገነናዊ ስርአዐቶች ውስጥ ዜጎች አማራጭ ወይም ነፃ የመረጃ መንገዳቸው በገዥዎች ስለሚታፈን ያላቸው መረጃ አገዛዙ የሰጠው ወይ የፈቀደው ብቻ ነው የሚሆነው።  የኢሳት አማራጭ የመረጃ ምንጭነት  ቢያንስ ሁሉንም ወገን የሚያስማማ ይመስለኛል አገዛዙ የጋረደውን የመረጃ መጋረጃ በመግፈፍ ከአገዛዙ ፍላጎት ውጪ ያሉ ዜናዎች፤ መረጃዎችና፤ ሃሳቦች በነፃነት እንዲንሽራሸሩ አድርጎዋል ወደፊትም ለማድረግ እየደከመ ያለ ተቋም በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ኢሳትን በገንዘብ በቁሳቁስ በሃሳብ ሊረዳ ይገባዋል።

ጸሃፊውን በዚህ ኢሜል ይገኛል [email protected]

ኢትዬጵያ ለዘላለም ትኑር!