0
Posted March 17, 2014 in Amharic news
 
 

በሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላትና አመራር ላይ በየካቲት 29 2006 ዓ.ም የተወስደውን እርምጃ በመቃወም ከዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የተሰጠ አቋም መግለጫ!


ድርጅታችን ከቆመላችው አንዱና ዋነኛ አላማ፣ በአገራችን ስላምና እኩልነትን ማስፈን መሆኑ ይታወቃል ሆኖም ገዢው ብድን የአለም የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በተደረገው ሩጫ ውድድር ላይ የስማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት በመገኘት ፈጹም ዴሞክራስያዊ በሆነ መንገድ በሥርዓቱ ምን ያህል እንደተማረሩ ድምፃቸውን ከፍ አድረገው ጮኸዋል፤ ዘምረዋል፣ በአካል ንቅናቄም አሳይተዋል ፣ ተቃውሞውን ተከትሎ ህግና ስርአትን ባልተከተለ መልኩ ውድ ሴት እህቶቻችን ወደ አስቃቂው ወያኔ እስር ቤት በየካቲት 29  2006 ቀን ግፍ በተሞላበት ሁኔታ ታፍነው ተወስደዋል::

ሆኖም በቆራጥ ሴት ወጣት የስማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች እጅጉን ኮርተናል ፣ የፍትህ እና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችውን ምንም ያህል ጭቆና በነገስበት ስርአት ውስጥ ቢሆኑም ሴቶች የለውጥ ምእራፍን ለመክፈት ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋእትነት ለመክፈል መዘጋጀታችውን ያሳዬበት ደማቅ ቀን መሆኑን አይተናል::

ይህንንም ኢፍትሃዊ ፣ አጸያፊና ፣ ስብአዊ መብትን የሚጻረር ድርጊት ባልተመረጠ መንግስት መፈጸሙ አዲስ ባይሆንም ድርጅታችን በአልበገር ባዮቹ ስማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት ላይ የተወስደውን እርምጃ  ከመቼውም በላይ አምርሮ ይቃወመዋል ፣ የዚህንም ፋሽት ስርአት ፍጸሜ ለማቅረብ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ከአባላቶቹ ጋር በመተባር ጠንክረን ከወትሮው በላቀ ንቃትና አንድነት እንድንታገለው ጥሪ ያደርጋል ::

 ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

 የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ

ኖርዌይ፣ ኦስሎ፣ መጋቢት 8 ፣ 2006