0
Posted January 23, 2013 in News
 
 

የእርቅ አባቶች እራሳቸዉ መታረቅ አቃታቸዉ- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ሲኖዶስ አሁንም ለሁለት እንደተከፈለ ነዉ


አገር ዉስጥና አገር ዉጭ በሚል ወያኔ ለሁለት የከፈለዉን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ሲኖዶስ አንድ ለማድረግ የተጀመረዉ ጥረት በወያኔ ጣልቃ ገብነት የተነሳ መክሸፉንና ከወያኔ አገዛዝ ጋር እጅና ጓንት የሆኑ አባቶች ተሰባስበዉ 6ኛዉን ፓትሪያሪክ መርጠዉ ለመሾም ዝግጅት መጀመራቸዉን አገር ቤት ላለዉ ሲኖደስ ቅርበት ያላቸዉ ምንጮቻችን ገለጹ። የዉጭዉ ሲኖዶስ ብጹዕ አቡነ መርቆሬዎስ አላግባብ የተቀሙት የፓትሪያሪክ ስልጣን ሊመለስላቸዉ ይገባል የሚል ጠንካራ አቋም ያለዉ ሲሆን አገር ዉስጥ ያለዉ ሲኖዶስ ግነ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በክብር አንዲኖሩ የቀረበዉን ሀሳብም አልቀበለም በማለቱ ሁለቱን ሲኖዶሶች ለማቀራረብ የተጀመረዉ ሽምግልና ያለ ዉጤት ተፈጽሟል።

ይህ በእንዲሀ እንዳለ በውጪ ሃገር የሚገኘው ሲኖዶስ በአገር ውስጥ የሚደረግን የፓትርያርክ ምርጫ ያወገዘ ሲሆን እርቀ-ሰላሙ ያልተሳካውም ሆነ የፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው የመመለስ ጉዳይ ተቀባይነት ያላገኘው ቤተ-ክርስቲያንን ለማጥፋት ቆርጦ በተነሳው ኢህአዴግ የተባለ ሀይል ምክንያት ነው ሲል አስታውቋል።

በስደት ያለው ሲኖዶስ  “ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ”በሚል ርዕስ ባወጣው ባለ 7 ገጽ መግለጫ ላይ፤ አራተኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ በከፍተኛ ባለስልጣናትና ትዕዛዝ በወታደሮች ተገደው እንዴት ከቦታቸው እንዲነሱ እንደተደረጉ በስፋትና በጥልቀት አብራርቷል፥ ፣ሀቁ ይህ በሆነበት ሁኔታ የአገር ቤቱ ሲኖዶስ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ አራተኛው ፓትርያርክ፦”ስላመመኝ ስልጣኔን ተረከቡኝ ብለዋል>> ማለቱ ፈጽሞ ውሸት መሆኑን ያመለከተው በስደት ያለው ሲኖዶስ፤አንዲትም የድምጽ፣ የወረቀትም ሆነ የምስል ማስረጃ ማቅረብ በማይቻልበት ሁኔታ ህዝብን በሀሰት ማደናገሩ አግባብ እንዳልሆነ መክሯል። እርቀ ሰላሙ እንዲሳካ ላለፉት ሶስት ዓመታት በራሳቸው ተነሳሽነት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ለቆዩት የቤተ ክርስቲያኗ ልጆች ጥልቅ ምስጋናውን ያቀረበው ሲኖዶሱ፤ አሁንም የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ከአገር ጉዳይ ተለይቶ የማይታይ በመሆኑ ሀገርን የምትወዱ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከሲኖዶሱ ጎን እንድትቆሙ ጥሪ እናቀርባለን ብሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ አዲስ አበባ ዉስጥ ያለዉ ሲኖዶስ የእርቅ ድርድሩ ያለዉጤት መጠናቀቁንና 6ኛዉን ፓትሪያሪክ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስመልክቶ ያወጣዉ መግለጫ ኢትዮጰያን ጨምሮ በመላዉ አለም የሚገኙትን የተዋህዶ እምነት ተከታዮች እያነጋገረ መሆኑ ታወቋል። ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑትና ወያኔ በግፍ 12 አመት በእስር ያንገላታቸዉ አባ አመሃ እየሱስ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ፣ በአዲስ አበባ ያለው እርቅ ያልተሳካው የሀይማኖት አባቶቹ የመንግስት ቅጥረኞች በመሆናቸው ነውም፣ ብለዋል።