0
Posted October 15, 2012 in Amharic news
 
 

ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተ መንግስቱን ሊለቁ ተስማሙ !!!


 

ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከቤተ መንግስት እንዲወጡ የቀረበላቸውን ጥያቄ ቢቀበሉም ጥርሳቸዉን እንደነከሱ ነው::ለሃይለማርያም ቤተመንግስቱን አላስረክብም በማለት ብትደነፋም አስቸኩዋይ የሚል ደብዳብይ ከደረሳት በሁዋላ ደንግጣለች::

በተለያዩ ምክንያቶች በመደርደር ላለመውጣት  አንድ ጊዜ ለደህንነቴ አይመችም ሌላ ግዜ ተዝካር ላውጣና …እያለች ምክንያቶች ብታበዛም ግፊቱ ስለጨመረባት ለመልቀቅ ተስማምታለች::ከቀረቡላት 3ቪላዎች ዉስጥ ከአራተኛ ክፍለ ጦር በታች ጠበንጃ ያዥ አከባቢ ወደ ዉስጥ ገባ ብሎ ከዚህ ቀደም የመለስ ዜናዊ አክስት ልጅ የጦር ጄኔራል የነበረው የዮሃንስ መኖሪያ ቤት ሊሰጣት እንደሆነ ምንጮች ተናግረዋል::

ይህ መኖሪያ ቤት ከዚህ ቀደም ያማር ክልል መሪ አያሌው ጎበዜ በቁም እስር ታስሮበት የነበር ሲሆን ባከባቢው በርካታ ባለስልጣናት ስለሚኖሩበት ጥበቃው ለደህንነት አያሰጋም ::በቅርቡም ከቤተመንግስት ተወጣለች ተብሏል እንደምንጮቹ ዘገባ ከሆነ የቤተመንግስቱን መልቀቅ ቅሬታ ቢፈጥርባትም ከመልቀቅ ሌላ አማራጭ እንደሌላት ገልጠዋል ።

የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ያረጋገጡ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ማለዳ ታይምስ እና እንዲሁም ምንጮች እንዳስረገጡት ከሆነ ወ/ሮ አዜብ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ናት የህወሃት ድርጅት ጋር ሊኖራት የሚችለው አጋርነት የሚያበቃ ይመስላል ይላሉ “እፉኝት “እያሉ የሚጠሯት ህወሃቶች አሁንም ነድፋ እንዳትገላቸው ፍራቻቸውም እነሱም ጋር ማየሉ እና ማንን ልትልክ እንደምትችል ስለማይታወቅ ከፍተኛውን የበቀል ድርሻ ልትወጣ ትችላለች ተብሏል ።

አዜብ በ እንደዚህ አይነት የበቀል እርምጃ ወስጧ የተካነችበት በመሆኑ በከፍተኛ ደረጃ አመራር አካላቶችም ይህንን ሰለሚያቁ ክፉኛ እንደሚጠሏት እና እንደሚፈሯት ይገልጻሉ ለሟቹ መለስ ሲሉ አክብረዋት ለዘመናት አብራቸው እንደኖረችም ያውቁታል ከአሁን በኋላ ላለው የኢፈርትም ሆነ የትእምኒት ወይም ሌሎች የአመራር ቦታ ላይ ምንም አይነት የስልጣን ቦታ ሊኖራት የማይችልበት ምክንያቶችን በማመቻቸት እና ማደላደል ላይ እንደሆኑ ምንጮች ይጠቁማሉ።

ከጥቂት ጊዜያት በኋላ በማግለል ወይንም እንደማናቸውም አባሎቻቸው ዘብጥያ በመወርወር ፣ወይንም ከሃገር በማባረር ካልተቻለም ደግሞ እንደአቦይ ስብሃት የውጭ ታዛቢ አድርገው ሊያስቀምጣት ይችላሉ ሲሉ ግምታቸውን ሰጥተዋል። እንደዚህ አይነት ችግሮቻቸውን ሰለሚያውቁ እና ለዚህም ሲባል ይመስላል ወ/ሮ አዜብ ቤተመንግስቱን አለቅም ሲሉ ሙግት የጀመሩት ።