0
Posted August 21, 2015 in Ginbot 7
 
 

ግንቦት 7 መሆን ያኮራል ፣ ከጀግኖች መቀላቀል ለሃገር ክብር መሰዋት መሆን፣ ለህዝብ ነፅነት መሞት ..


ግንቦት 7 መሆን ያኮራል ፣  ከጀግኖች መቀላቀል ለሃገር ክብር መሰዋት መሆን፣  ለህዝብ ነፅነት መሞት፣  የተዘናበለውን የኢትዮጽያ ባንዲራ በመስዋዕትነታችን ማንሳት ፣ የነሽብሬን የነብዩን ደም መመለስ  ፣ ከጀርናም ጀግና  የሚያስኝ  ሳይተኩስ የሚገድል ገናና  መንፈስ ያለው የአሽናፊነት ራእይ የሰነቀ ድርጅት ስም  ።

በጠላታችው እጅ ወድቀው እንካን  ለእናት አገር ሲባል ማን ይፈራል በማለት  ስቃያችውን ግርፋታችውን ድል ያደረጉበትን ፋርጣማ  ራእይ ለህዝባችው ያካፈሉት እየሩሳሌም ተስፋው ፥ብርሃኑ ተ/ያሬድ እና  ፍቅረማርያም አስማማውን ደብዳቤ በመንተራስ ጥቂት እላለሁ ሳሊ አብረሃም

አረንጓዴ ቢጫ ቀይ  ባንዲራችን  የጅግንነት ምልክት ፣ ህዝቦችዋም የነጻነት ፈርጥ ሆነው ለዘመናት ቢኖሩም  የታሪክ መዛግብት ላይ የስፈረችው ኢትዬጲያ  ዛሬ ካለንባት አገር ጋር ምንም ቁርኝት ያላት በማይመስል መልኩ  ማንነታችንን ተገፈናል ፣ እርቃናችንን የቆምን ያህል እንዲህ የተዋረድንበት ወቅት አይኖርም ፣ እውነትን  ሃቀኝነትን ታማኝነት እና ሃገር ወዳድነትን  ከድም ስራችን ለማውጣት ቆርጦ የተነሳው ወያኔ ፍትህን እና ስልጣን  ለአጎብዳጆች  ፣ እድገትን ለሆድ አዳሮዎች  በማስረከብ ሃቀኛው ህብረተስብ  ጦሙን እንዲያድር እና ተስፋ እንዲቆርጥ በማድረግ የበይ ተመልካች ከምሆን የሚል ስጋዊ ፍላጎት አስገድዶት  ለስርአቱ መዝለቅ እጃዙር ተባባሪ ለመሆን  ተገድዋል ።

አሁንም የኋው ጨቆኝ ስርአት ምን አገባኝ የሚል አስተሳስብን ለማስረጽ  ማስፈራራትን  ግርፋትን እንግልትን እና  እስር ለማበራከት ጠንክሮ በመስራቱ ይህ ነው የማይባል ተጸእኖ ወጣቱ  ህብረተስብ ላይ አሳድሮዋል  ።  ይህንንም ክፍተት የተማመኑ የወያኔ ሹማምንቶች ስልጣናችው ላይ ተደላድለው  ጉብ ባሉበት ወቅት ይህ ከስደድ እሳት የሚልቅ አግራዊ አስተሳስብ ከነዝህ ጠፉ የሉም ቢገፊዋችው አይነሱም ከተባሉ ወጣቶች ብቅ ማለቱ ለወያኔዎች እጅግ አስደንጋጭ እንደሚሆንባችው ጥያቄ የለውም።

እነዚህ እስከወድያኛው ሞት ካልሆነ አያቆመንም ያሉ ወጣቶች ስርአቱን ከመጎንተል ያልተናነስ ነው ያሉትን ትግል ለማሳካት እየሩሳሌም ተስፋው 7 ግዜ  ፥ ብርሃኑ ተ/ያሬድ  19 ግዜ እና  ፍቅረማርያም አስማማው  ለ9 ግዜ ለእስር  እንደተዳረጉ  አስታውስው ለስርአቱ ማብቂያ ፣  ለአግራዊ ውርደታችን ልጓም ፣ ለመጪው ትውልድ የዴሞክራሲ እኩልነት ራእይ ያነገበውን ግንቦት 7ን  ለመቀላቀል መወስናችው ስሜታዊ ሳይሆን ምክንያታዊ መሆኑን በግልጽ ያስቀመጡበት መልእክታችው በርካታ  ነጥቦችን ያነሳል ከሁሉ በላይ መልእክቱን ይዘት ያነበበ  ሁሉ በስርአቱ መዳፍ ወድቀው ስቃይ የሚቆጥሩ ሳይሆን ጠላታችውን በግንባር ገጥመው ለመፋለም በቂ ትጥቅ ያነገቱ ወታደሮች ያስመስላችዋል፣   እውነት ነው ጠላታችን ወያኔ መስሪነት እንጂ ህጸናትን ማታለል የሚይችል የሞራል ብቃት እንዳሌለው የስርአቱ ጋሽ አጃግሬዎችም በትክክል ይረዱታል የህወሃት ወላጅ አባቶች የሚባሉትም ቢሆኑ የራስችው ድምጸ አስተጋብቶ እያሞኛችው መሆኑን የገባችው አይመስልም ።

ፓርላማ ተብዬ  የወንበር ቤርጎ ግንቦት 7  ታሽብሩናላችሁ ያሉበት ዋና ምክንያት የድርጅቱ  አላማ  እና  ብቃት ጥሩ የተደላደለ መስረት እንዳለው ጠቋሚ ሲሆን ይህ የዳቦ ስም በተደጋጋሚ ሲስተጋባ  የሚስማው በአንድ ፈርጁ የምእራባውያንን  ቀልብ ሊስብ ከቻለ በሚል እሳቤ ነበር ቢሆም ውጤት አልባ  ሆኖ  ቆይቶዋል ሆኖም  አንዳንድ ኢትዬጲያውያን ወገኖቻችን ግንቦት 7 የሚለው የድርጅቱ ስም  በራሱ ስር የስደደ ስጋት ሲጭርባችው  ይስተዋላል  ። ይህ ሰሜት በወያኔ ቁና  ከመስፈር  ስጋት  የመነጨ እንጂ የድርጅቱን አቋም ጥያቄ ውስጥ ያስገባ  አይደለም

በጥቅሉ  እነዝህ 3 ወጣቶች በልበሙሉነት እነዚህን ሁሉ ቅርንጫፎች አጥርተው አንድ ጠንካራ አላማ ላይ በመቆም  በፋና ወጊነቱ ታሪክ ያስታውሳችዋል

“ምርጫችን  ሁሉን አቀፍ ትግል መርጦ ለአግር ነጻነት የሚታገለው አግራችንን ከፋሽታዊ አግዛዝ ነጻ ለማውጣት ሌት ተቀን ሞትን ተጋፍጠው የሚተጉ አባላትንና ትግሉን ስኬታማ  ለማድረግ በለበ ሙሉነት ለስልጣን ሳይሆን ለሞት የሚሽቀዳደሙ መሪዋች ወደተስባስቡበት በአግዛዙ ፓርላማ አሽባር የሚል የዳቦ ስም  ወደ ተስጠው  ግንቦት 7  ወደተስኘው ነጻ አውጪ ድርጅት ድርጅት አደረግን  ድንቅ ምርጫ  ! መቼም የማንጸጸትበት  ሁሌም በኩራት ደጋግመን ምርጫ !!“

እኛም ነገ በገሃድ ግንቦት 7 ነን ማለትን ከማለት አልፈን የልጃችንን ሆነ የድርጅታችን  ስም ግንቦት 7  ብለን በመስየም የነዚህን ወጣቶች ድፍረት እና  ጸናት በስፋት ህዝባችንን እንደምናላብስ ጥርጥር የለውም

ታሳሪዊቹ የግንቦት 7 ነን ምስክርነታችው ክሳችውንና  ስቃያችውን እጥፍ ድርብ እንደሚያደርገው በትክክል ቢረዱትም ከመዳረሻችው ያስተጓጎላችው ወያኔ ስጋችውን እንጂ ራእያችውን ማስተጎል እንደማይችል አሳይተውናል ዱካችው በርካቶችን እንደሚጠራም ሳይታለም የተፈታ  ነው ግን  እነዚህ ትንታግ ወጣቶች ለትግሉ ግንባር ቢበቁ ኖሮ  ባነሱት ስይፍ የሚስነዝሩት ጥቃት በአይነ ህሊናችሁ ሳሉት ………………

ኢትዮጲያችን መቼም ጀግና   ደሃ ሆና  አታውቅም!!

ዴሴሶን ራዲዮ / DCESON RADIO

ሳሊ አብረሃም