0
Posted January 17, 2013 in Featured
 
 

ታላቅ የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በኖርዎይ ኦስሎ


ስማ!! ያገሬ ሰው በኦስሎ ከተማ ፌብርዋሪ 10፥2013 በ16፥00 ሰዓት ( ልብ ይሏል ባገርኛው ከተሲዓት ነው ) እንገናኝ ተብሎ ተቀጥሯል፥ አደራ እንዳትቀር ያገሬ ሰው የቀረህ እንደው ማርያምን እጣላሃለው፥ እክል ገጥሞህ ሳይመችህ ቢቀር እንኳን ካርኒ በመግዛት መደጎም እንደምትችል እንዳትዘነጋ፥፥

 
ወጉ ለኢሳት የኢትዮጵያውያን ጆሮ ማሰባሰቢያ ነው፥፥ 
 
እንዳትቀር ያገሬ ሰው፥፥
 
ኽበር ማለፊያ 200 የኖርዎይ ገንዘብ ያዝ፥ ለምትለግሰውም ጨመር አርገህ ያዝ፣፥
 
ካርኒውን ኸኢቶጵያውያን ማህበር፥ ኽዲሞክራቲክ ቼንጅ የድጋፍ ድርጅት፥ ለጥቆም ኽአበሻ የባህል ሱቅ በመምጣት መገብየት ትችላለህ፥፥
 
ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ