0
Posted October 13, 2014 in Amharic news
 
 

የወያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ቴዎድሮች አድሃኖም በኦስሎ ተዋረዱ!


ዴሴሶን ራዲዮ
ኦክቶበር 11 2014
ተግባር የማንነት ምልክት ይሆናል ንግግር ወይም ጸሁፍ የአስተሳስብ ብስለትን ወይም ክስረትን ያሳያል ። የአገራችንን ስልጣን ተዋረድ ከላይ እስከታች እንመራለን የሚሉ ግለስቦችን ስናይ ግን በአስተሳ ሰባቸው ሳይሆን በሎሌነታችው፣ በማልማታችው ሳይሆን ፍጽም ርህራሄ አልባነታች ተመርጠው ወደ በትረ ስልጣ ሲሽጋገሩ ይታያሉ ።
ይህን ሁኔታ ሞች ጠ/ሚ በግልጸ አስታውቀዋል አክለውም የዛፍ ላይ እንቅልፍ መሆኑንም አልሽሽጉም በተግባርም የበረሃ ጎዶቻቸውን ሳይቀር ንብረታችውን ቀምተው ስልጣናችውን ገፈው በአፋቸው ውርደታቸውን እንዲያውጁ ተገደው የወህኒ እራት የሆኑ አያሌ ናችው በስፈሩት ቁና መስፈራቸው እንደማያበሳጫቸው እገምታለሁ
ወደ ጎብኝያችን አቶ ተዬድሮስ አድሃኖም ስመለስም በአስመራ ዩኒቨርሲቲ የባዮሎጂ ተማሪ እንደነበሩ ይወሳላቸዋል በጤናው ዘርፍ ብዙ አስተዋጸኦ አበርክዋል ተብለው ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒትርነት በመንጠላጠል በህወሃት ስርአት ውስጥ የሚያስጋቸው ነገር እንደማይኖር የሚያስቡ ይመስለኛል፣ ቀለም አስተሳስብን ይገራል የሚለው አመለካከት በዚህ ስው ላይ ገንቢ ውጤት እንዳላስከተለ ዋቢ መጥቀስ አያሻም ።
የወያኔ የውጭጉዳይ ሚኒቴርም ከአለም ሀያላን ስር ስር እየሮጡ ከኪሳችው በሚያወጡት የሁለት አሃዝ እድገት ድርስት እውን እያስመስሉ መተወን ስለተካኑበት ትወናቸውም በወያኔ እጅግ ተወዶላቸው የሜዲያ ስርከስ የሚባለውን የማምታታት ተውኔት በመሪ ተዋናኝነቱን እያከናወኑ ይገኛሉ። ሲሻቸው በዘፈን ሲሻቸው በጊታር ደግሞም የህዝብ ተቆርቋሪም ለመምስል ከተፈናቃይ ወገኖቻችን ጋር መአድ በመቅረብ ድራማውን እያሳመሩ ይታያሉ ፣ በድራማው የሚታለል ከተገኘ ማለቴ ነው ! ሆኖም ግን የአገራችን ህዝብ እነዚህን መስል ማጭበርበሪያዎች አያጣችውም
በሌላው አቅጣጫ ደግሞ በምስራቅ አፍሪካ ላይ በዘረፋ እና ሙስና ቀዳሚ ተሳታፊ ከሆኑት አገራትም የምንኖርባት ኖርዎይ አንድዋ ነች ፡ ኖርዌይ በስላምዋ በደህንነትዋ ህዝቦችዋ ጠግበው ከሚያድሩባቸው አገራት የመጀመሪያ ረድፍ መሆንዋ ከወንጀለኞች ጋር እንዳታብር ምንም ተጸእኖ አላሳደረም ይባስ የኢትዮጲያ ህዝብ የአገሩን ሀብት ተጠቃሚ እንዳይሆን ሙስናን ከሚያስፋፉ ኩባንያዎች አንዱም ያራ የሚባለው በኖርዌይ ይሚገኘ የማዳበሪያ አምራች ኩባንያ ሲሶው ሃብት የመንግስት እንደሆነ ይነገራል ።
ያራ በሊቢያ በህንድ እና በራሻ በፈጸማችው ወይም ባስፈጸማችው የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል 48 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት እንደሚጣልባችው ተነግሮዋል ሆኖም ይህ ኩባንያ ወንጀሉን ከብዙ አመታት በፊት የፈጸሙት በመሆኑ ክሱ እና ቅጣቱ የሚያመጣው ውጤት እይኖርም የሙስናው ተጠቂ ግን የታዳጊ አገር ህዝቦች ናቸው ።
ከዚህም መስል ምዝበራዎች ታዳጊ አግሮችን የሚታደጉበትን ቅደመ ሁኔታ ባለመቀመጣቸው በቀጣይ ለሚደረጉ የንግድ ግንኙነቶች ሚዛናዊነት አንዳች ማረጋገጫ የለም
ለሟች ጠቅላይ ሚኒስትራችንም በገሃድ የተስጠው እጅ መንሻ ገንዘብ ጥያቄ ውስጥ አለማገባቱ ! ይህን ተከትሎ የተፈጸሙ ውሎች አለመመርመራቻው ! ወደፊት የሚደረጉ ግንኙነትቶች ህግን የተከተሉ እንደማይሆኑ መገመት ያስችላል
ወያኔ ይህንን ሁኔታ በመረዳቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩን በመላክ ይህን የሱን እኩይ ተግባር የሚተባበሩት ስብእናችውን የሽጡ ኩባንያዎችን ለማጥመድ አያሌ የስላም ውሎች የተፍረሙባት በኦስሎ ከተማ ላይ የፊታችን ሃሙስ ኦክቶበር 16 ቀነ ቀጠሮ ቆርጠዋል ለቆራጥ ታጋዮችም ይህ ምን ማለት እንደሆነ ትንተና እንዳማሻው እገምታለሁ
እኛ በስደት ኖርዌይ የምንገኝ ወገኖች ሊያንገበግበን የሚገባ ነገር ቢኖር በኖርዌይ ምድር አንድ ዛፍ ለመቁረጥ ብዙ ህግጋቶችንና ጥንቃቄዎችን ሲያመሳክሩ ይታያሉ ግን እናት አገራችን ኢትዮጵያ ህዝቦችዋ ሲገፋ፣ ሲታስሩ ፣ሲፋናቀሉ እያዩ አላየንም የሚሉ ምእራባውያንና ኩባንያዎቻችው ከህዝብ በተነጠቀ መሬት ላይ ስራቸውን እያጧጧፉ ኪሳችውን ማደለባችው ከተጠያቂነት አንደማያድናቸው ልናስታውቃችው ይገባል ! ብሎም ከአሁን በኋላ የተቃውሞችን አፈሙዛችን ወደነሱም ማዞር ይኖርበናል እላለሁ።
ሳሊ አብረሃም